-
2 ሳሙኤል 12:8-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 የጌታህን ቤት ልሰጥህ፣+ የጌታህንም ሚስቶች+ በእቅፍህ ላደርግልህ ፈቃደኛ ነበርኩ፤ የእስራኤልንና የይሁዳንም ቤት ሰጠሁህ።+ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የበለጠ ነገር ላደርግልህ ፈቃደኛ ነበርኩ።+ 9 ታዲያ በፊቱ መጥፎ ነገር በመሥራት የይሖዋን ቃል ያቃለልከው ለምንድን ነው? ሂታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታኸው!+ በአሞናውያን ሰይፍ ከገደልከውም+ በኋላ ሚስቱን ወስደህ ሚስትህ አደረግካት።+ 10 ስለዚህ የሂታዊውን የኦርዮን ሚስት ወስደህ ሚስትህ በማድረግ እኔን ስለናቅክ ሰይፍ ከቤትህ ፈጽሞ አይለይም።’+
-