ዘፍጥረት 39:10-12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እሷም ዮሴፍን በየቀኑ ትወተውተው ነበር፤ እሱ ግን ከእሷ ጋር ለመተኛትም ሆነ አብሯት ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አልሆነም። 11 ይሁንና አንድ ቀን ዮሴፍ ሥራውን ለማከናወን ወደ ቤት ሲገባ ከቤቱ አገልጋዮች መካከል አንዳቸውም በዚያ አልነበሩም። 12 እሷም ልብሱን አፈፍ አድርጋ ይዛ “አብረኸኝ ተኛ!” አለችው። እሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ። ምሳሌ 6:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ትእዛዙ መብራት ነውና፤+ሕጉም ብርሃን ነው፤+የተግሣጽ ወቀሳም ወደ ሕይወት ይመራል።+ 24 ከክፉ ሴት፣+ ከባለጌ* ሴትምየሚያባብል አንደበት ይጠብቁሃል።+ ምሳሌ 7:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ጥበብን “እህቴ ነሽ” በላት፤ ማስተዋልንም “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፤ 5 ጋጠወጥና*+ ባለጌ* ከሆነች ሴት፣እንዲሁም ከምትናገረው የሚያባብል* ቃል ይጠብቁሃል።+
10 እሷም ዮሴፍን በየቀኑ ትወተውተው ነበር፤ እሱ ግን ከእሷ ጋር ለመተኛትም ሆነ አብሯት ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አልሆነም። 11 ይሁንና አንድ ቀን ዮሴፍ ሥራውን ለማከናወን ወደ ቤት ሲገባ ከቤቱ አገልጋዮች መካከል አንዳቸውም በዚያ አልነበሩም። 12 እሷም ልብሱን አፈፍ አድርጋ ይዛ “አብረኸኝ ተኛ!” አለችው። እሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ወደ ውጭ ሸሽቶ ወጣ።