19 ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፦ “አይዟችሁ አትፍሩ። ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው? 20 ምንም እንኳ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ የነበረ ቢሆንም+ አምላክ ግን ይኸው ዛሬ እንደምታዩት ነገሩን ለመልካም አደረገው፤ የብዙ ሰዎችንም ሕይወት ለማዳን ተጠቀመበት።+ 21 ስለሆነም አትፍሩ። ለእናንተም ሆነ ለትናንሽ ልጆቻችሁ የሚያስፈልገውን እህል እሰጣችኋለሁ።”+ እሱም በዚህ መንገድ አጽናናቸው፤ እንዲሁም አረጋጋቸው።