ዘዳግም 32:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 በቀልም ሆነ ቅጣት የእኔ ነው፤+አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ሲደርስ እግራቸው ይከዳቸዋል፤+የሚጠፉበት ቀን ቀርቧልና፤የሚጠብቃቸውም ነገር በፍጥነት ይመጣል።’ ምሳሌ 24:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 “እሱ እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ፤እንደ ሥራው እከፍለዋለሁ”* አትበል።+ ማቴዎስ 5:38, 39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 “‘ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ’+ እንደተባለ ሰምታችኋል። 39 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ክፉን ሰው አትቃወሙት፤ ከዚህ ይልቅ ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሌላኛውን ደግሞ አዙርለት።+ ሮም 12:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ለማንም በክፉ ፋንታ ክፉ አትመልሱ።+ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ጥረት አድርጉ። ሮም 12:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ከዚህ ይልቅ “‘በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ’ ይላል ይሖዋ”*+ ተብሎ ስለተጻፈ ለቁጣው* ዕድል ስጡ።+ 1 ተሰሎንቄ 5:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ማንም ሰው በማንም ላይ በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤+ ከዚህ ይልቅ እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ምንጊዜም መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።+
38 “‘ዓይን ስለ ዓይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ’+ እንደተባለ ሰምታችኋል። 39 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ክፉን ሰው አትቃወሙት፤ ከዚህ ይልቅ ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሌላኛውን ደግሞ አዙርለት።+
19 የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ከዚህ ይልቅ “‘በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ’ ይላል ይሖዋ”*+ ተብሎ ስለተጻፈ ለቁጣው* ዕድል ስጡ።+
15 ማንም ሰው በማንም ላይ በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤+ ከዚህ ይልቅ እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ ምንጊዜም መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።+