ዘኁልቁ 23:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ከዚያም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከአራም፣+ከምሥራቅ ተራሮች አመጣኝ፤ ‘ና፣ ያዕቆብን እርገምልኝ። አዎ ና፣ እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ።+ 8 አምላክ ያልረገመውን እኔ እንዴት ልረግም እችላለሁ? ይሖዋ ያላወገዘውንስ እኔ እንዴት ላወግዝ እችላለሁ?+ ምሳሌ 19:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ሰው በልቡ ብዙ ነገር ያቅዳል፤የሚፈጸመው ግን የይሖዋ ፈቃድ* ነው።+ የሐዋርያት ሥራ 5:38, 39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 ስለዚህ አሁን የምላችሁ፣ እነዚህን ሰዎች አትንኳቸው፤ ተዉአቸው። ይህ ውጥን ወይም ይህ ሥራ ከሰው ከሆነ ይጠፋል፤ 39 ከአምላክ ከሆነ ግን ልታጠፏቸው አትችሉም።+ እንዲያውም ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”+
7 ከዚያም ይህን ምሳሌያዊ አባባል ተናገረ፦+ “የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ከአራም፣+ከምሥራቅ ተራሮች አመጣኝ፤ ‘ና፣ ያዕቆብን እርገምልኝ። አዎ ና፣ እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ።+ 8 አምላክ ያልረገመውን እኔ እንዴት ልረግም እችላለሁ? ይሖዋ ያላወገዘውንስ እኔ እንዴት ላወግዝ እችላለሁ?+
38 ስለዚህ አሁን የምላችሁ፣ እነዚህን ሰዎች አትንኳቸው፤ ተዉአቸው። ይህ ውጥን ወይም ይህ ሥራ ከሰው ከሆነ ይጠፋል፤ 39 ከአምላክ ከሆነ ግን ልታጠፏቸው አትችሉም።+ እንዲያውም ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”+