ዘፍጥረት 11:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ይሖዋም እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ ናቸው፤+ ይኸው አሁን ደግሞ ይህን መሥራት ጀምረዋል። በዚህ ከቀጠሉ ያሰቡትን* ሁሉ ከማከናወን የሚያግዳቸው ምንም ነገር አይኖርም። 7 ና! እንውረድና*+ በቋንቋ እርስ በርስ እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እናዘበራርቅ።” ዘፍጥረት 50:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፦ “አይዟችሁ አትፍሩ። ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው? 20 ምንም እንኳ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ የነበረ ቢሆንም+ አምላክ ግን ይኸው ዛሬ እንደምታዩት ነገሩን ለመልካም አደረገው፤ የብዙ ሰዎችንም ሕይወት ለማዳን ተጠቀመበት።+ ምሳሌ 21:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 ይሖዋን የሚጻረር ጥበብ፣ ማስተዋልም ሆነ ምክር ከንቱ ነው።+ ዳንኤል 4:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 የምድር ነዋሪዎች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማያት ሠራዊትና በምድር ነዋሪዎች ላይ እንደ ፈቃዱ ያደርጋል። ሊያግደው* ወይም ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚችል ማንም የለም።+ የሐዋርያት ሥራ 5:38, 39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 ስለዚህ አሁን የምላችሁ፣ እነዚህን ሰዎች አትንኳቸው፤ ተዉአቸው። ይህ ውጥን ወይም ይህ ሥራ ከሰው ከሆነ ይጠፋል፤ 39 ከአምላክ ከሆነ ግን ልታጠፏቸው አትችሉም።+ እንዲያውም ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”+
6 ይሖዋም እንዲህ አለ፦ “እነዚህ ሰዎች አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ ናቸው፤+ ይኸው አሁን ደግሞ ይህን መሥራት ጀምረዋል። በዚህ ከቀጠሉ ያሰቡትን* ሁሉ ከማከናወን የሚያግዳቸው ምንም ነገር አይኖርም። 7 ና! እንውረድና*+ በቋንቋ እርስ በርስ እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እናዘበራርቅ።”
19 ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፦ “አይዟችሁ አትፍሩ። ለመሆኑ እኔን በአምላክ ቦታ ያስቀመጠኝ ማን ነው? 20 ምንም እንኳ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ የነበረ ቢሆንም+ አምላክ ግን ይኸው ዛሬ እንደምታዩት ነገሩን ለመልካም አደረገው፤ የብዙ ሰዎችንም ሕይወት ለማዳን ተጠቀመበት።+
35 የምድር ነዋሪዎች ሁሉ እንደ ኢምንት ይቆጠራሉ፤ በሰማያት ሠራዊትና በምድር ነዋሪዎች ላይ እንደ ፈቃዱ ያደርጋል። ሊያግደው* ወይም ‘ምን ማድረግህ ነው?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚችል ማንም የለም።+
38 ስለዚህ አሁን የምላችሁ፣ እነዚህን ሰዎች አትንኳቸው፤ ተዉአቸው። ይህ ውጥን ወይም ይህ ሥራ ከሰው ከሆነ ይጠፋል፤ 39 ከአምላክ ከሆነ ግን ልታጠፏቸው አትችሉም።+ እንዲያውም ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”+