ምሳሌ 22:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ልጅን* ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው፤+በሚያረጅበት ጊዜም እንኳ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።+ ምሳሌ 22:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ሞኝነት በልጅ* ልብ ውስጥ ታስሯል፤+የተግሣጽ በትር ግን ከእሱ ያርቀዋል።+ ምሳሌ 23:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ልጅን* ከመገሠጽ ወደኋላ አትበል።+ በበትር ብትመታው አይሞትም። ኤፌሶን 6:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 አባቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁን አታስመርሯቸው፤+ ከዚህ ይልቅ በይሖዋ* ተግሣጽና+ ምክር* አሳድጓቸው።+