ዘዳግም 15:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በልግስና ስጠው፤+ ስትሰጠው ልብህ ቅር እያለው መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በሥራህ ሁሉና በምታከናውነው በማንኛውም ነገር የሚባርክህ በዚህ የተነሳ ነው።+ 11 መቼም ቢሆን ከምድሪቱ ላይ ድሆች አይጠፉምና።+ ‘በምድርህ ላይ ለሚኖር ጎስቋላና ድሃ ወንድምህ በልግስና እጅህን ዘርጋለት’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው።+ ምሳሌ 19:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ለችግረኛ ሞገስ የሚያሳይ ለይሖዋ ያበድራል፤+ላደረገውም ነገር ብድራት* ይከፍለዋል።+ ሉቃስ 14:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውራንን ጥራ፤+ 14 ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ። ምክንያቱም በጻድቃን ትንሣኤ+ ብድራት ይመለስልሃል።” ዕብራውያን 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አምላክ ቅዱሳንን በማገልገልም* ሆነ ወደፊትም ማገልገላችሁን በመቀጠል የምታከናውኑትን ሥራ እንዲሁም ለስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር+ በመርሳት ፍትሕ አያዛባም።
10 በልግስና ስጠው፤+ ስትሰጠው ልብህ ቅር እያለው መሆን የለበትም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ በሥራህ ሁሉና በምታከናውነው በማንኛውም ነገር የሚባርክህ በዚህ የተነሳ ነው።+ 11 መቼም ቢሆን ከምድሪቱ ላይ ድሆች አይጠፉምና።+ ‘በምድርህ ላይ ለሚኖር ጎስቋላና ድሃ ወንድምህ በልግስና እጅህን ዘርጋለት’ በማለት ያዘዝኩህ ለዚህ ነው።+
13 ሆኖም ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ ሽባዎችን፣ አንካሶችንና ዓይነ ስውራንን ጥራ፤+ 14 ብድር ሊመልሱልህ ስለማይችሉ ደስተኛ ትሆናለህ። ምክንያቱም በጻድቃን ትንሣኤ+ ብድራት ይመለስልሃል።”