መዝሙር 37:21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ክፉ ሰው ይበደራል፤ መልሶም አይከፍልም፤ጻድቅ ሰው ግን ለጋስ ነው፤* ደግሞም ይሰጣል።+ ሉቃስ 6:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል።+ ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።” 2 ቆሮንቶስ 9:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ+ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው* ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ።+ 1 ጢሞቴዎስ 6:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 በተጨማሪም መልካም ነገር እንዲያደርጉ፣ በመልካም ሥራዎች ባለጸጋ እንዲሆኑ እንዲሁም ለጋሶችና ለሌሎች ለማካፈል ዝግጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፤+
38 ለሰዎች ስጡ፤ እነሱም ይሰጧችኋል።+ ተትረፍርፎ እስኪፈስ ድረስ በተጠቀጠቀና በተነቀነቀ ጥሩ መስፈሪያ ሰፍረው በእቅፋችሁ ይሰጧችኋል። በምትሰፍሩበት መስፈሪያ መልሰው ይሰፍሩላችኋልና።”