መዝሙር 112:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለቅኖች በጨለማ ውስጥ እንደ ብርሃን ያበራል።+ ח [ኼት] ሩኅሩኅና* መሐሪ+ እንዲሁም ጻድቅ ነው። ኢሳይያስ 9:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 በጨለማ ውስጥ ይሄዱ የነበሩ ሰዎችታላቅ ብርሃን አዩ። ድቅድቅ ጨለማ ባጠላበት ምድር የሚኖሩ ሰዎችምብርሃን ወጣላቸው።+ ሉቃስ 1:68 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 68 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ* ፊቱን ወደ ሕዝቡ ስለመለሰና ሕዝቡን ስላዳነ+ ውዳሴ ይድረሰው።+ ሉቃስ 1:79 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 79 ይኸውም በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ+ ለተቀመጡት ብርሃን ለመስጠት እንዲሁም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ለመምራት ነው።”