13 ከዚያም ከናዝሬት ወጥቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አውራጃዎች፣ በባሕሩ አጠገብ ወደምትገኘው ወደ ቅፍርናሆም+ መጥቶ መኖር ጀመረ፤ 14 ይህም የሆነው በነቢዩ ኢሳይያስ የተነገረው የሚከተለው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፦ 15 “ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ ወደ ባሕሩ በሚወስደው መንገድ አጠገብ ያላችሁ የዛብሎን ምድር፣ የንፍታሌም ምድርና የአሕዛብ ገሊላ ሆይ! 16 በጨለማ ውስጥ ያሉ ሰዎች ታላቅ ብርሃን አዩ፤ ሞት በሰዎች ላይ ባጠላበት ምድር ላሉም ብርሃን+ ወጣላቸው።”+