ዘሌዋውያን 16:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤+ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው* ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል። 22 ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ+ ወደ በረሃ ይሄዳል፤+ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።+ 1 ጴጥሮስ 2:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እሱ ራሱ በገዛ አካሉ ኃጢአታችንን በእንጨት* ላይ+ ተሸከመ።+ ደግሞም “በእሱ ቁስል እናንተ ተፈወሳችሁ።”+ 1 ዮሐንስ 2:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የተወደዳችሁ ልጆቼ፣ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ኃጢአት* እንዳትሠሩ ነው። ማንም ኃጢአት ቢሠራ ግን በአብ ዘንድ ረዳት* አለን፤ እሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።+ 2 እሱ ለእኛ ኃጢአት+ የቀረበ የማስተሰረያ* መሥዋዕት ነው፤+ ሆኖም ለእኛ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ኃጢአት ጭምር ነው።+
21 ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤+ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው* ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል። 22 ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ+ ወደ በረሃ ይሄዳል፤+ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።+
2 የተወደዳችሁ ልጆቼ፣ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ኃጢአት* እንዳትሠሩ ነው። ማንም ኃጢአት ቢሠራ ግን በአብ ዘንድ ረዳት* አለን፤ እሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።+ 2 እሱ ለእኛ ኃጢአት+ የቀረበ የማስተሰረያ* መሥዋዕት ነው፤+ ሆኖም ለእኛ ኃጢአት ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ኃጢአት ጭምር ነው።+