ሮም 8:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 እነሱን የሚኮንን ማን ነው? ምክንያቱም የሞተው ብሎም ከሞት የተነሳውና በአምላክ ቀኝ የተቀመጠው+ እንዲሁም ስለ እኛ የሚማልደው+ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። 1 ጢሞቴዎስ 2:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አንድ አምላክ አለና፤+ በአምላክና በሰው መካከል+ ደግሞ አንድ መካከለኛ አለ፤+ እሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤+ ዕብራውያን 7:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ስለሆነም ለእነሱ ለመማለድ ሁልጊዜ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእሱ አማካኝነት ወደ አምላክ የሚቀርቡትን ፈጽሞ ሊያድናቸውም ይችላል።+