ኢሳይያስ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በሬ ጌታውን፣አህያም የባለቤቱን ጋጣ በሚገባ ያውቃል፤እስራኤል ግን እኔን* አላወቀም፤+የገዛ ሕዝቤም አላስተዋለም።” ኤርምያስ 2:32 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 ለመሆኑ አንዲት ድንግል ጌጣጌጧን፣ሙሽሪትስ ጌጠኛ መቀነቷን* ትረሳለች? የገዛ ሕዝቤ ግን ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ቀናት ረስቶኛል።+ ኤርምያስ 9:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ምላሳቸውን እንደ ደጋን ወጠሩ፤በምድሪቱ ላይ ታማኝነት ሳይሆን ውሸት ሰፍኗል።+ “በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤እኔንም ጨርሶ አይሰሙም”+ ይላል ይሖዋ።
3 ምላሳቸውን እንደ ደጋን ወጠሩ፤በምድሪቱ ላይ ታማኝነት ሳይሆን ውሸት ሰፍኗል።+ “በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤እኔንም ጨርሶ አይሰሙም”+ ይላል ይሖዋ።