የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 56:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድና

      የእሱ አገልጋዮች ለመሆን

      ከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+

      ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣

      ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣

       7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+

      በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ።

      የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ።

      ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+

  • ኢሳይያስ 66:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 የእስራኤል ልጆች በንጹሕ ዕቃ ስጦታ ይዘው ወደ ይሖዋ ቤት እንደሚያመጡ፣ ወንድሞቻችሁን ሁሉ ለይሖዋ ስጦታ እንዲሆኑ ከየብሔራቱ በፈረሶች፣ በሠረገሎች፣ ጥላ ባላቸው ጋሪዎች፣ በበቅሎዎችና በፈጣን ግመሎች ጭነው ወደተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጧቸዋል”+ ይላል ይሖዋ።

  • ሕዝቅኤል 20:40
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 40 “‘በቅዱሱ ተራራዬ፣ ከፍ ባለውም የእስራኤል ተራራ ላይ፣’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ፣ ‘መላው የእስራኤል ቤት ሰዎች፣ አዎ ሁሉም በዚያ በምድሪቱ ላይ ያገለግሉኛልና።+ በዚያም በእነሱ ደስ እሰኛለሁ፤ ደግሞም ቅዱስ ከሆኑት ነገሮቻችሁ ሁሉ መዋጮዎቻችሁንና የመባችሁን የፍሬ በኩራት እሻለሁ።+

  • ኢዩኤል 3:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 እናንተም እኔ በተቀደሰው ተራራዬ+ በጽዮን የምኖር አምላካችሁ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ።

      ኢየሩሳሌም ቅዱስ ስፍራ ትሆናለች፤+

      እንግዶችም* ከእንግዲህ በእሷ አያልፉም።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ