ኢሳይያስ 1:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ሰማያት ሆይ፣ ስሙ፤ ምድር ሆይ፣ አድምጪ፤+ይሖዋ እንዲህ ሲል ተናግሯልና፦ “ወንዶች ልጆችን ተንከባክቤ አሳደግኩ፤+እነሱ ግን በእኔ ላይ ዓመፁ።+ ኢሳይያስ 31:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ እጅግ ወዳመፃችሁበት አምላክ ተመለሱ።+ ኢሳይያስ 59:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሕግ ተላልፈናል፤ ይሖዋንም ክደናል፤ለአምላካችን ጀርባችንን ሰጥተናል። ግፍንና ዓመፅን ተናግረናል፤+በልባችን ውሸትን ፀንሰናል፤ እንዲሁም የሐሰት ቃላትን አጉተምትመናል።+
13 ሕግ ተላልፈናል፤ ይሖዋንም ክደናል፤ለአምላካችን ጀርባችንን ሰጥተናል። ግፍንና ዓመፅን ተናግረናል፤+በልባችን ውሸትን ፀንሰናል፤ እንዲሁም የሐሰት ቃላትን አጉተምትመናል።+