9 አንቺ ለጽዮን ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣+
ከፍ ወዳለ ተራራ ውጪ።
አንቺ ለኢየሩሳሌም ምሥራች የምትነግሪ ሴት ሆይ፣
ድምፅሽን በኃይል ከፍ አድርጊ።
ድምፅሽን ከፍ አድርጊ፤ አትፍሪ።
ለይሁዳ ከተሞች “እነሆ፣ አምላካችሁ” በማለት አስታውቂ።+
10 እነሆ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ በኃይል ይመጣል፤
ክንዱም ስለ እሱ ይገዛል።+
እነሆ፣ የሚከፍለው ወሮታ ከእሱ ጋር ነው፤
የሚመልሰውም ብድራት በፊቱ አለ።+