ኢሳይያስ 7:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በመሆኑም ይሖዋ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፦ እነሆ፣ ወጣቷ* ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤+ አማኑኤል* ብላም ትጠራዋለች።+ ኢሳይያስ 7:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ልጁ ክፉውን መጥላትና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት በጣም የምትፈራቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ጨርሶ የተተወ ይሆናል።+ ኢሳይያስ 8:3, 4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 እኔም ከነቢዪቱ* ጋር ተገናኘሁ፤* እሷም ፀነሰች፤ በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች።+ ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው፤ 4 ልጁ ‘አባዬ!’ እና ‘እማዬ!’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወሰዳል።”+
3 እኔም ከነቢዪቱ* ጋር ተገናኘሁ፤* እሷም ፀነሰች፤ በኋላም ወንድ ልጅ ወለደች።+ ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ “ስሙን ማኸር-ሻላል-ሃሽ-ባዝ ብለህ ጥራው፤ 4 ልጁ ‘አባዬ!’ እና ‘እማዬ!’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወሰዳል።”+