-
ሉቃስ 1:30-35አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 ስለዚህ መልአኩ እንዲህ አላት፦ “ማርያም ሆይ፣ በአምላክ ፊት ሞገስ ስላገኘሽ አትፍሪ። 31 እነሆም፣ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤+ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።+ 32 እሱም ታላቅ ይሆናል፤+ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤+ ይሖዋ* አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤+ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”+
34 ማርያም ግን መልአኩን “እኔ ከወንድ ጋር ግንኙነት ፈጽሜ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” አለችው።+ 35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤+ የልዑሉም ኃይል በአንቺ ላይ ያርፋል። ስለሆነም የሚወለደው ልጅ ቅዱስና+ የአምላክ ልጅ+ ይባላል።
-