መዝሙር 137:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 137 በባቢሎን ወንዞች አጠገብ፣+ በዚያ ተቀምጠን ነበር። ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።+ ኢሳይያስ 14:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በባቢሎን ንጉሥ ላይ እንዲህ ብለህ ትተርታለህ፦* “ሌሎችን አስገድዶ ሲያሠራ የነበረው* እንዴት አበቃለት! ጭቆናውስ እንዴት አከተመ!+ ኢሳይያስ 14:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 መላዋ ምድር አርፋለች፤ ከረብሻም ነፃ ሆናለች። ሕዝቦች በደስታ እልል ብለዋል።+ ኢሳይያስ 35:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ፤+ ወደ ጽዮንም በእልልታ ይመጣሉ።+ ፍጻሜ የሌለው ደስታን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ ደስታንና ሐሴትን ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከዚያ ይርቃሉ።+
10 ይሖዋ የዋጃቸው ይመለሳሉ፤+ ወደ ጽዮንም በእልልታ ይመጣሉ።+ ፍጻሜ የሌለው ደስታን እንደ አክሊል ይጎናጸፋሉ።+ ደስታንና ሐሴትን ያገኛሉ፤ሐዘንና ሲቃም ከዚያ ይርቃሉ።+