ኢሳይያስ 13:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ከመንግሥታትም ሁሉ እጅግ የከበረችው፣*+የከለዳውያን ውበትና ኩራት የሆነችው ባቢሎን፣+አምላክ እንደገለበጣቸው እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ትሆናለች።+ ዕንባቆም 1:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እነሆ፣ ጨካኝና ፈጣን የሆነውን ብሔር ይኸውምከለዳውያንን አስነሳለሁና።+ የእነሱ ያልሆኑ ቤቶችን ለመውረስ፣ሰፋፊ የምድር ክፍሎችን ይወራሉ።+