15 “የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እነሆ፣ በሩቅ ቦታ ያለን ብሔር አመጣባችኋለሁ”+ ይላል ይሖዋ።
“እሱም ለረጅም ጊዜ የኖረ ብሔር ነው።
ከጥንት ዘመን ጀምሮ የነበረ፣
ቋንቋውን የማታውቀውና
ንግግሩን የማትረዳው ብሔር ነው።+
16 የፍላጻ ኮሮጇቸው እንደተከፈተ መቃብር ነው፤
ሁሉም ተዋጊዎች ናቸው።
17 እነሱ አዝመራህንና ምግብህን ይበላሉ።+
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን ይበላሉ።
መንጎችህንና ከብቶችህን ይበላሉ።
የወይን ተክሎችህንና የበለስ ዛፎችህን ይበላሉ።
የምትታመንባቸውን የተመሸጉ ከተሞችህን በሰይፍ ያወድማሉ።”