መዝሙር 46:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 46 አምላክ መጠጊያችንና ብርታታችን፣+በጭንቅ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስልን ረዳታችን ነው።+ ናሆም 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋ ጥሩ ነው፤+ በጭንቀትም ቀን መሸሸጊያ ነው።+ እሱን መጠጊያ ማድረግ የሚፈልጉትን ያውቃል።*+ ሶፎንያስ 3:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 እኔም ትሑት የሆነና ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሕዝብ በመካከላችሁ እንዲቀር አደርጋለሁ፤+እነሱም የይሖዋን ስም መጠጊያቸው ያደርጉታል።