12 በዚያን ጊዜ የባላዳን ልጅ የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ቤሮዳክባላዳን ሕዝቅያስ መታመሙን ሰምቶ ስለነበር ደብዳቤና ስጦታ ላከለት።+ 13 ሕዝቅያስም ለመልእክተኞቹ ጥሩ አቀባበል አደረገላቸው፤ ከዚያም ግምጃ ቤቱን ሁሉ ይኸውም ብሩን፣ ወርቁን፣ የበለሳን ዘይቱን፣ ሌላውን ምርጥ ዘይት፣ የጦር መሣሪያውንና በግምጃ ቤቶቹ ውስጥ ያለውን ንብረት በሙሉ አሳያቸው።+ ሕዝቅያስ በቤቱም ሆነ በግዛቱ ሁሉ ያላሳያቸው ምንም ነገር አልነበረም።