2 ነገሥት 19:35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 35 በዚያም ሌሊት የይሖዋ መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች ገደለ።+ ሰዎችም በማለዳ ሲነሱ ሬሳውን አዩ።+ ኢሳይያስ 14:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 አሦራዊውን በምድሬ ላይ አደቀዋለሁ፤በተራሮቼም ላይ እረግጠዋለሁ።+ ቀንበሩ ከላያቸው ላይ ይነሳል፤ሸክሙም ከትከሻቸው ላይ ይወርዳል።”+ ሶፎንያስ 2:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እሱ እጁን ወደ ሰሜን ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌንም ባድማና እንደ በረሃ ደረቅ ያደርጋታል።+