የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ዜና መዋዕል 32:21, 22
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 21 ከዚያም ይሖዋ አንድ መልአክ ልኮ በአሦር ንጉሥ ሰፈር የነበሩትን ኃያላን ተዋጊዎች+ እንዲሁም መሪዎችና አለቆች ሁሉ ጠራርጎ አጠፋ፤ ንጉሡም ኀፍረት ተከናንቦ ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ። በኋላም ወደ አምላኩ ቤት ገባ፤* በዚያም ሳለ የገዛ ወንዶች ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት።+ 22 በዚህ መንገድ ይሖዋ ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅና ከሌሎች ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካሉ ጠላቶቻቸው ሁሉ እረፍት ሰጣቸው።

  • ኢሳይያስ 30:31
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 31 ከይሖዋ ድምፅ የተነሳ አሦር በሽብር ይናጣልና፤+

      በበትርም ይመታዋል።+

  • ኢሳይያስ 31:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  8 አሦራዊውም የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፤

      የሰው ያልሆነም ሰይፍ ይበላዋል።+

      እሱም ሰይፉን ፈርቶ ይሸሻል፤

      ወጣቶቹም የግዳጅ ሥራ ይሠራሉ።

  • ኢሳይያስ 37:36, 37
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 36 የይሖዋም መልአክ ወጥቶ በአሦራውያን ሰፈር የነበሩትን 185,000 ሰዎች ገደለ። ሰዎችም በማለዳ ሲነሱ ሬሳውን አዩ።+ 37 በመሆኑም የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከዚያ ተነስቶ ወደ ነነዌ+ ተመለሰ፤ በዚያም ተቀመጠ።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ