ኢሳይያስ 48:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 አዎ፣ አንተ አልሰማህም፤+ አላወቅክምም፤ከዚህ በፊት ጆሮህ ክፍት አልነበረም። በጣም አታላይ እንደሆንክና+ከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ዓመፀኛ ተብለህ እንደተጠራህ አውቃለሁና።+ ኤርምያስ 3:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እናንተ ግን ባሏን* ክዳ እንደምትሄድ ሚስት በእኔ ላይ ክህደት ፈጽማችኋል’+ ይላል ይሖዋ።” ሆሴዕ 5:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እነሱ ይሖዋን ከድተዋል፤+ባዕድ ወንዶች ልጆች ወልደዋልና። አሁንም አንድ ወር፣ እነሱንና ድርሻቸውን* ይውጣል።* ሆሴዕ 6:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እነሱ ግን እንደ ተራ ሰዎች ቃል ኪዳኑን ተላለፉ።+ በዚያም እኔን ከዱኝ።
8 አዎ፣ አንተ አልሰማህም፤+ አላወቅክምም፤ከዚህ በፊት ጆሮህ ክፍት አልነበረም። በጣም አታላይ እንደሆንክና+ከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ዓመፀኛ ተብለህ እንደተጠራህ አውቃለሁና።+