2 ነገሥት 25:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን+ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ 9 እሱም የይሖዋን ቤት፣+ የንጉሡን ቤትና*+ በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ የታዋቂ ሰዎችንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አጋየ።+ 2 ዜና መዋዕል 36:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 የእውነተኛውን አምላክ ቤት አቃጠለ፤+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ፤+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እንዲሁም ውድ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ አወደመ።+ ኢሳይያስ 63:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ቅዱስ ሕዝብህ ለጥቂት ጊዜ ወርሶት ነበር። ጠላቶቻችን መቅደስህን ረግጠዋል።+ ኢሳይያስ 64:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 አባቶቻችን አንተን ያወደሱበትየቅድስናና የክብር ቤታችን*በእሳት ተቃጥሏል፤+ከፍ አድርገን እንመለከታቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ ፈራርሰዋል።
8 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በሰባተኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን+ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ 9 እሱም የይሖዋን ቤት፣+ የንጉሡን ቤትና*+ በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ የታዋቂ ሰዎችንም ቤቶች ሁሉ በእሳት አጋየ።+
19 የእውነተኛውን አምላክ ቤት አቃጠለ፤+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ፤+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እንዲሁም ውድ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ አወደመ።+