46 “ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከምሥራቅ ትይዩ የሆነው የውስጠኛው ግቢ በር+ በስድስቱ የሥራ ቀናት+ ዝግ እንደሆነ ይቆይ፤+ ሆኖም በሰንበት ቀንና አዲስ ጨረቃ በምትወጣበት ቀን ይከፈት። 2 አለቃው ከውጭ በኩል በበሩ በረንዳ ገብቶ+ በበሩ መቃን አጠገብ ይቆማል። ካህናቱ የእሱን ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ እሱም በበሩ ደፍ ላይ ይሰግዳል፤ ከዚያም ይወጣል። በሩ ግን እስከ ምሽት ድረስ አይዘጋ።