ኤርምያስ 24:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ።+ በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ+ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+ ኤርምያስ 31:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+ ኤርምያስ 32:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 ለእነሱም ሆነ ከእነሱ በኋላ ለሚመጡት ልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ዘወትር እኔን እንዲፈሩ+ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።+
33 “ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና” ይላል ይሖዋ። “ሕጌን በውስጣቸው አኖራለሁ፤+ በልባቸውም እጽፈዋለሁ።+ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”+