የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ነገሥት 11:5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ሰለሞን የሲዶናውያንን እንስት አምላክ አስታሮትንና+ አስጸያፊ የሆነውን የአሞናውያንን አምላክ ሚልኮምን+ ተከተለ።

  • 1 ነገሥት 11:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ሰለሞን አስጸያፊ ለሆነው የሞዓብ አምላክ ለከሞሽና አስጸያፊ ለሆነው ለአሞናውያን+ አምላክ ለሞሎክ+ ኢየሩሳሌም ፊት ለፊት በሚገኘው ተራራ ላይ ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ+ የሠራው በዚህ ጊዜ ነበር።

  • መዝሙር 106:35, 36
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 35 ይልቁንም በዚያ ከነበሩት ብሔራት ጋር ተቀላቀሉ፤+

      የእነሱንም መንገድ ተከተሉ።*+

      36 ጣዖቶቻቸውን አመለኩ፤+

      እነሱም ወጥመድ ሆኑባቸው።+

  • ኢሳይያስ 57:7, 8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 በረጅሙና ከፍ ባለው ተራራ ላይ አልጋሽን አነጠፍሽ፤+

      መሥዋዕት ለማቅረብም ወደዚያ ወጣሽ።+

       8 ከበሩና ከመቃኑ ጀርባ የመታሰቢያ ምልክትሽን አደረግሽ።

      እኔን ተውሽኝ፤ እርቃንሽንም ገለጥሽ፤

      ወደ ላይ ወጣሽ፤ መኝታሽንም አሰፋሽ።

      ከእነሱም ጋር ቃል ኪዳን ገባሽ።

      በአልጋቸው ላይ አብረሽ መተኛት ወደድሽ፤+

      የወንድ ብልትም* አፍጥጠሽ አየሽ።

  • ኤርምያስ 2:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 ‘ከረጅም ጊዜ በፊት ቀንበርሽን ሰባበርኩ፤+

      የታሰርሽበትንም ሰንሰለት በጣጠስኩ።

      አንቺ ግን “አንተን አላገለግልም” አልሽ፤

      ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይና ቅጠሉ በተንዠረገገ ዛፍ ሁሉ ሥር+

      ለማመንዘር ተንጋለሽ ተኝተሻልና።+

  • ያዕቆብ 4:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 አመንዝሮች ሆይ፣* ከዓለም ጋር መወዳጀት ከአምላክ ጋር ጠላትነት መፍጠር እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ ራሱን የአምላክ ጠላት ያደርጋል።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ