ዘዳግም 28:49, 50 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ 50 ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው።+ ኤርምያስ 4:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እነሆ፣ እሱ ዝናብ እንዳዘሉ ደመናት ይመጣል፤ሠረገሎቹም እንደ አውሎ ነፋስ ናቸው።+ ፈረሶቹ ከንስር ይበልጥ ፈጣኖች ናቸው።+ ጠፍተናልና ወዮልን! ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 አሳዳጆቻችን በሰማይ ከሚበርሩ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ነበሩ።+ በተራሮች ላይ አጥብቀው አሳደዱን፤ በምድረ በዳ አድፍጠው አጠቁን።
49 “ይሖዋ ቋንቋውን የማትረዳውን+ በሩቅ ያለን አንድ ብሔር ከምድር ጫፍ አስነስቶ ያመጣብሃል፤+ እሱም እንደ ንስር ተምዘግዝጎ ይወርድብሃል፤+ 50 ይህ ብሔር ለሽማግሌ የማያዝን ወይም ለወጣት የማይራራ ፊቱ የሚያስፈራ ብሔር ነው።+