ኤርምያስ 37:7, 8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔን እንድትጠይቁ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ “እነሆ፣ እናንተን ለመርዳት የመጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብፅ ይመለሳል።+ 8 ከለዳውያኑም ተመልሰው መጥተው ይህችን ከተማ ይወጓታል፤ ይይዟታልም፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።”+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 4:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 አሁንም እንኳ እርዳታ እናገኛለን ብለን በከንቱ ስንጠባበቅ ዓይኖቻችን ደከሙ።+ ሊያድነን ከማይችል ብሔር እርዳታ ለማግኘት ስንጠባበቅ ቆየን።+ ሕዝቅኤል 29:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በዚያን ጊዜ የግብፅ ነዋሪዎች ሁሉ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ፤ለእስራኤል ቤት ከአገዳ* የተሻለ ድጋፍ መሆን አልቻሉምና።+
7 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔን እንድትጠይቁ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ “እነሆ፣ እናንተን ለመርዳት የመጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብፅ ይመለሳል።+ 8 ከለዳውያኑም ተመልሰው መጥተው ይህችን ከተማ ይወጓታል፤ ይይዟታልም፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።”+