5 በዚህ ጊዜ የፈርዖን ሠራዊት ከግብፅ ወጥቶ ነበር፤+ ኢየሩሳሌምን ከበው የነበሩት ከለዳውያንም ይህን ሰሙ። በመሆኑም ኢየሩሳሌምን ለቀው ሄዱ።+ 6 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ ነቢዩ ኤርምያስ መጣ፦ 7 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘እኔን እንድትጠይቁ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ “እነሆ፣ እናንተን ለመርዳት የመጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ አገሩ ወደ ግብፅ ይመለሳል።+