ዘፀአት 23:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 “ጉቦ አትቀበል፤ ምክንያቱም ጉቦ አጥርተው የሚያዩ ሰዎችን ዓይን ያሳውራል፤ እንዲሁም የጻድቅ ሰዎችን ቃል ሊያዛባ ይችላል።+ ዘዳግም 27:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “‘ንጹሑን ሰው* ለመግደል ሲል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን።’+ (ሕዝቡም ሁሉ ‘አሜን!’ ይላል።) ኢሳይያስ 1:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 አለቆችሽ ግትሮችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው።+ ሁሉም ጉቦ የሚወዱና እጅ መንሻ የሚያሳድዱ ናቸው።+ አባት የሌለው ልጅ ፍትሕ እንዲያገኝ* አያደርጉም፤የመበለቲቱም አቤቱታ ወደ እነሱ አይደርስም።+
23 አለቆችሽ ግትሮችና የሌባ ግብረ አበሮች ናቸው።+ ሁሉም ጉቦ የሚወዱና እጅ መንሻ የሚያሳድዱ ናቸው።+ አባት የሌለው ልጅ ፍትሕ እንዲያገኝ* አያደርጉም፤የመበለቲቱም አቤቱታ ወደ እነሱ አይደርስም።+