ዘፀአት 32:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ላይ ሳይወርድ እንደቆየ አየ።+ በመሆኑም አሮንን ከበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ በል ተነስተህ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን።”+ ዘፀአት 32:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እሱም ወርቁን ከእነሱ ወስዶ በቅርጽ ማውጫ ቅርጽ አወጣለት፤ የጥጃ ሐውልትም* አድርጎ ሠራው።+ እነሱም “እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” ይሉ ጀመር።+ 1 ነገሥት 12:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው። 2 ነገሥት 10:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ሆኖም የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኃጢአት ይኸውም በቤቴልና በዳን ከነበሩት የወርቅ ጥጆች+ ጋር በተያያዘ እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ያደረገውን ኃጢአት ከመከተል ዞር አላለም።
32 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ላይ ሳይወርድ እንደቆየ አየ።+ በመሆኑም አሮንን ከበው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ያ ሙሴ ምን እንደደረሰበት ስለማናውቅ በል ተነስተህ ከፊት ከፊታችን የሚሄድ አምላክ ሥራልን።”+
4 እሱም ወርቁን ከእነሱ ወስዶ በቅርጽ ማውጫ ቅርጽ አወጣለት፤ የጥጃ ሐውልትም* አድርጎ ሠራው።+ እነሱም “እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው” ይሉ ጀመር።+
28 በመሆኑም ንጉሡ ከተማከረ በኋላ ሁለት የወርቅ ጥጃዎችን+ ሠርቶ ሕዝቡን “ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት መንገላታት ይሆንባችኋል። እስራኤል ሆይ፣ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ይኸውልህ” አለ።+ 29 ከዚያም አንደኛውን በቤቴል+ ሌላኛውን ደግሞ በዳን+ አቆመው።
29 ሆኖም የናባጥን ልጅ የኢዮርብዓምን ኃጢአት ይኸውም በቤቴልና በዳን ከነበሩት የወርቅ ጥጆች+ ጋር በተያያዘ እስራኤላውያን እንዲፈጽሙ ያደረገውን ኃጢአት ከመከተል ዞር አላለም።