የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 3:18-23
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 በዚያ ቀን ይሖዋ ጌጦቻቸውን ሁሉ ይነጥቃል፦

      አልቦውን፣ የፀጉር ጌጡን፣ የጨረቃ ቅርጽ ያለውን ጌጥ፣+

      19 የጆሮ ጉትቻውን፣* አምባሩን፣ መከናነቢያውን፣

      20 የራስ መሸፈኛውን፣ የሰንሰለት አልቦውን፣ ጌጠኛውን መቀነት፣*

      የሽቶ ዕቃውን፣* ክታቡን፣

      21 የጣት ቀለበቱን፣ የአፍንጫ ቀለበቱን፣

      22 የክት ልብሱን፣ መደረቢያውን፣ ካባውን፣ የእጅ ቦርሳውን፣

      23 የእጅ መስተዋቱን፣+ የበፍታ ልብሶቹን፣*

      ጥምጥሙንና መከናነቢያውን ይወስድባቸዋል።

  • ኤርምያስ 4:30
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 30 ለጥፋት ተዳርገሻል፤ ታዲያ ምን ታደርጊ ይሆን?

      ደማቅ ቀይ ልብስ ትጎናጸፊ፣

      በወርቅ ጌጣጌጦች ታጌጪና

      ዓይኖችሽን ትኳዪ ነበር።

      ይሁንና ትዋቢ የነበረው እንዲያው በከንቱ ነው፤+

      በፍትወት ስሜት ይከተሉሽ የነበሩት ትተውሻልና፤

      አሁን ሕይወትሽን* ይሿታል።+

  • ሕዝቅኤል 16:39
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 39 በእጃቸው አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤ እነሱም ጉብታዎችሽን ያፈርሳሉ፤ ከፍ ያሉ ቦታዎችሽንም ያወድማሉ፤+ ልብሶችሽንም ይገፉሻል፤+ ያማሩ ጌጣጌጦችሽንም ይወስዳሉ፤+ እርቃንሽንና ራቁትሽንም ያስቀሩሻል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ