36 ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከፍቅረኞችሽና የወንዶች ልጆችሽን ደም መሥዋዕት አድርገሽ ካቀረብሽላቸው+ አስጸያፊና ቀፋፊ ጣዖቶችሽ+ ሁሉ ጋር ባመነዘርሽ ጊዜ ከልክ በላይ በፍትወት ስለተቃጠልሽና እርቃንሽ ስለተገለጠ፣ 37 እኔ ደስ ያሰኘሻቸውን ፍቅረኞችሽን ሁሉ፣ የወደድሻቸውንም ሆነ የጠላሻቸውን ሁሉ አንድ ላይ እሰበስባለሁ። እነሱን ከየቦታው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ እርቃንሽን ለእነሱ እገልጣለሁ፤ እነሱም ሙሉ በሙሉ እርቃንሽን ሆነሽ ያዩሻል።+