መዝሙር 115:4-7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+ 5 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤ 6 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤ 7 እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤+በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።+ ኢሳይያስ 46:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ከኮሮጇቸው ወርቅ የሚዘረግፉ ሰዎች አሉ፤ብሩን በሚዛን ይመዝናሉ። አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ እሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል።+ እነሱም በፊቱ ይደፋሉ፤ ደግሞም ያመልኩታል።*+ 7 አንስተው ትከሻቸው ላይ ያደርጉታል፤+ተሸክመው ወስደው ቦታው ላይ ያኖሩታል፤ በዚያም ዝም ብሎ ይቆማል። ካለበት ቦታ አይንቀሳቀስም።+ ወደ እሱ ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስም፤ማንንም ከጭንቀት ሊታደግ አይችልም።+
4 የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+ 5 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤ 6 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤ 7 እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤+በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።+
6 ከኮሮጇቸው ወርቅ የሚዘረግፉ ሰዎች አሉ፤ብሩን በሚዛን ይመዝናሉ። አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ እሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል።+ እነሱም በፊቱ ይደፋሉ፤ ደግሞም ያመልኩታል።*+ 7 አንስተው ትከሻቸው ላይ ያደርጉታል፤+ተሸክመው ወስደው ቦታው ላይ ያኖሩታል፤ በዚያም ዝም ብሎ ይቆማል። ካለበት ቦታ አይንቀሳቀስም።+ ወደ እሱ ይጮኻሉ፤ እሱ ግን አይመልስም፤ማንንም ከጭንቀት ሊታደግ አይችልም።+