ዳንኤል 2:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ስለዚህ ንጉሡ ሕልሞቹን እንዲነግሩት አስማተኞቹ ካህናት፣ ጠንቋዮቹ፣ መተተኞቹና ከለዳውያኑ* እንዲጠሩ አዘዘ። በዚህም መሠረት ገብተው በንጉሡ ፊት ቆሙ።+ ዳንኤል 4:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “በዚህ ጊዜ አስማተኞቹ ካህናት፣ ጠንቋዮቹ፣ ከለዳውያኑና* ኮከብ ቆጣሪዎቹ+ ገቡ። ያየሁትን ሕልም ስነግራቸው ትርጉሙን ሊያሳውቁኝ አልቻሉም።+ ዳንኤል 5:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 በዚህ ጊዜ የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ሆኖም ጽሑፉን ማንበብም ሆነ ትርጉሙን ለንጉሡ ማሳወቅ አልቻሉም።+