7 ንጉሡ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጠንቋዮቹን፣ ከለዳውያኑንና ኮከብ ቆጣሪዎቹን እንዲያመጧቸው አዘዘ።+ ንጉሡም የባቢሎንን ጠቢባን እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ጽሑፍ የሚያነብና ትርጉሙን የሚነግረኝ ማንኛውም ሰው ሐምራዊ ልብስ ይለብሳል፤ አንገቱ ላይ የወርቅ ሐብል ይደረግለታል፤+ በመንግሥትም ላይ ሦስተኛ ገዢ ይሆናል።”+
8 በዚህ ጊዜ የንጉሡ ጠቢባን ሁሉ ገቡ፤ ሆኖም ጽሑፉን ማንበብም ሆነ ትርጉሙን ለንጉሡ ማሳወቅ አልቻሉም።+