የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 13:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ምድሪቱን ስለ ክፋቷ፣+

      ክፉዎችንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ።

      የእብሪተኞችን ኩራት አጠፋለሁ፤

      የጨቋኞችንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።+

  • ኤርምያስ 25:12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 “‘ይሁንና ሰባው ዓመት ሲፈጸም+ በበደላቸው የተነሳ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ብሔር ተጠያቂ አደርጋለሁ’*+ ይላል ይሖዋ፤ ‘የከለዳውያንንም ምድር እስከ ወዲያኛው ባድማ አደርገዋለሁ።+

  • ኤርምያስ 27:6, 7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 6 አሁንም እነዚህን ሁሉ አገሮች ለአገልጋዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነጾር አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤+ የዱር አራዊትም እንኳ እንዲገዙለት አድርጌአለሁ። 7 የእሱ መንግሥት የሚያበቃበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ+ ብሔራት ሁሉ እሱን፣ ልጁንና የልጅ ልጁን ያገለግላሉ፤ በዚያን ጊዜ ግን ብዙ ብሔራትና ታላላቅ ነገሥታት ባሪያቸው ያደርጉታል።’+

  • ኤርምያስ 50:1, 2
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 50 ይሖዋ በነቢዩ ኤርምያስ በኩል ስለ ባቢሎን+ ይኸውም ስለ ከለዳውያን ምድር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦

       2 “በብሔራት መካከል ይህን ተናገሩ፤ ደግሞም አውጁ።

      ምልክት* አቁሙ፤ ይህን አውጁ።

      ምንም ነገር አትደብቁ!

      እንዲህም በሉ፦ ‘ባቢሎን ተይዛለች።+

      ቤል ኀፍረት ተከናንቧል።+

      ሜሮዳክ በፍርሃት ርዷል።

      ምስሎቿ ተዋርደዋል።

      አስጸያፊ የሆኑ ጣዖቶቿ* ተሸብረዋል።’

  • ኤርምያስ 51:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 “ፍላጻዎቻችሁን አሹሉ፤+ ክብ የሆኑትን ጋሻዎች አንሱ።*

      ይሖዋ የሜዶናውያንን ነገሥታት መንፈስ አነሳስቷል፤+

      ምክንያቱም ባቢሎንን ለማጥፋት አስቧል።

      ይህ የይሖዋ በቀል ይኸውም ስለ ቤተ መቅደሱ የሚወስደው የበቀል እርምጃ ነውና።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ