ዳንኤል 12:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “የዘወትሩ መሥዋዕት+ ከተቋረጠበትና ጥፋት የሚያመጣው ርኩስ ነገር ከቆመበት+ ጊዜ አንስቶ 1,290 ቀን ይሆናል። ማቴዎስ 24:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 “ስለዚህ ነቢዩ ዳንኤል በተናገረው መሠረት ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’ በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ስታዩ+ አንባቢው ያስተውል፤ ማርቆስ 13:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “ይሁንና ጥፋት የሚያመጣው ‘ርኩስ ነገር’+ በማይገባው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል፤ በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።+ ሉቃስ 21:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 “ይሁንና ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ስታዩ+ መጥፊያዋ እንደቀረበ እወቁ።+