ኢሳይያስ 58:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 58 “ጉሮሮህ እስኪሰነጠቅ ጩኽ፤ ምንም አትቆጥብ! ድምፅህን እንደ ቀንደ መለከት አሰማ። ለሕዝቤ ዓመፃቸውን፣ለያዕቆብ ቤት ኃጢአታቸውን አውጅ።+ ኤርምያስ 1:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከዚያም ይሖዋ እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ።+ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ።+ 10 እንግዲህ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድታወድም፣ እንድትገነባና እንድትተክል ዛሬ በብሔራትና በመንግሥታት ላይ ሾሜሃለሁ።”+ ሕዝቅኤል 3:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እነሆ፣ ፊትህን ልክ እንደ እነሱ ፊት ጠንካራ አድርጌዋለሁ፤ ግንባርህንም ልክ እንደ እነሱ ግንባር አጠንክሬዋለሁ።+ 9 ግንባርህን እንደ አልማዝ፣ ከባልጩትም ይበልጥ ጠንካራ አድርጌዋለሁ።+ አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር፤+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።”
9 ከዚያም ይሖዋ እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ።+ ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “ቃሌን በአፍህ አኑሬአለሁ።+ 10 እንግዲህ እንድትነቅልና እንድታፈርስ፣ እንድታጠፋና እንድታወድም፣ እንድትገነባና እንድትተክል ዛሬ በብሔራትና በመንግሥታት ላይ ሾሜሃለሁ።”+
8 እነሆ፣ ፊትህን ልክ እንደ እነሱ ፊት ጠንካራ አድርጌዋለሁ፤ ግንባርህንም ልክ እንደ እነሱ ግንባር አጠንክሬዋለሁ።+ 9 ግንባርህን እንደ አልማዝ፣ ከባልጩትም ይበልጥ ጠንካራ አድርጌዋለሁ።+ አትፍራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሳ አትሸበር፤+ እነሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።”