ኢሳይያስ 32:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ይህም የሚሆነው መንፈስ ከላይ እስኪፈስብን፣+ምድረ በዳውም የፍራፍሬ እርሻ እስከሚሆን፣የፍራፍሬ እርሻውም እንደ ጫካ እስከሚቆጠር ድረስ ነው።+ ኢሳይያስ 44:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ለተጠማው* ውኃ አፈሳለሁና፤+በደረቁ ምድርም ላይ ጅረቶች እንዲፈስሱ አደርጋለሁ። መንፈሴን በዘርህ ላይ፣በረከቴንም በልጅ ልጆችህ ላይ አፈሳለሁ።+ ሕዝቅኤል 39:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 ከእንግዲህ ፊቴን ከእስራኤል ቤት ሰዎች አልሰውርም፤+ በእነሱ ላይ መንፈሴን አፈሳለሁና’+ ይላል ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ።”