ዘፀአት 19:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 አሁንም ቃሌን በጥብቅ ብትታዘዙና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ መላው ምድር የእኔ ስለሆነ+ እናንተ ከሌሎች ሕዝቦች ሁሉ የተመረጣችሁ ልዩ ንብረቶቼ* ትሆናላችሁ።+ ዘዳግም 7:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+ መዝሙር 147:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ቃሉን ለያዕቆብ፣ሥርዓቱንና ፍርዶቹን ለእስራኤል ያስታውቃል።+ 20 ይህን ለሌላ ለማንም ብሔር አላደረገም፤+እነሱ ስለ ፍርዶቹ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። ያህን አወድሱ!*+
6 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+
19 ቃሉን ለያዕቆብ፣ሥርዓቱንና ፍርዶቹን ለእስራኤል ያስታውቃል።+ 20 ይህን ለሌላ ለማንም ብሔር አላደረገም፤+እነሱ ስለ ፍርዶቹ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። ያህን አወድሱ!*+