ኤርምያስ 20:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ስለዚህ “እሱን አላነሳም፤ከእንግዲህም በስሙ አልናገርም” አልኩ።+ ይሁንና ቃሉ በልቤ ውስጥ እንዳለ፣ በአጥንቶቼም ውስጥ እንደገባ የሚነድ እሳት ሆነብኝ፤አፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ከዚህ በላይ መቋቋም አልቻልኩም።+ አሞጽ 7:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በዚህ ጊዜ አሞጽ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ ከዚህ ይልቅ እረኛና+ የሾላ ዛፎች የምንከባከብ* ሰው ነኝ። 15 ይሖዋ ግን ከመንጋ ጠባቂነት ወሰደኝ፤ ይሖዋም ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ።+ የሐዋርያት ሥራ 4:19, 20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው እንዲህ አሏቸው፦ “አምላክን ከመስማት ይልቅ እናንተን መስማት በአምላክ ፊት ተገቢ እንደሆነና እንዳልሆነ እስቲ እናንተው ፍረዱ። 20 እኛ ግን ስላየነውና ስለሰማነው ነገር ከመናገር ወደኋላ ማለት አንችልም።”+
9 ስለዚህ “እሱን አላነሳም፤ከእንግዲህም በስሙ አልናገርም” አልኩ።+ ይሁንና ቃሉ በልቤ ውስጥ እንዳለ፣ በአጥንቶቼም ውስጥ እንደገባ የሚነድ እሳት ሆነብኝ፤አፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ከዚህ በላይ መቋቋም አልቻልኩም።+
14 በዚህ ጊዜ አሞጽ ለአሜስያስ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ነቢይ ወይም የነቢይ ልጅ አይደለሁም፤ ከዚህ ይልቅ እረኛና+ የሾላ ዛፎች የምንከባከብ* ሰው ነኝ። 15 ይሖዋ ግን ከመንጋ ጠባቂነት ወሰደኝ፤ ይሖዋም ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ።+
19 ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው እንዲህ አሏቸው፦ “አምላክን ከመስማት ይልቅ እናንተን መስማት በአምላክ ፊት ተገቢ እንደሆነና እንዳልሆነ እስቲ እናንተው ፍረዱ። 20 እኛ ግን ስላየነውና ስለሰማነው ነገር ከመናገር ወደኋላ ማለት አንችልም።”+