-
ዘዳግም 24:21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 “ከወይን እርሻህ ላይ የወይን ፍሬህን በምትሰበስብበት ጊዜ ተመልሰህ ቃርሚያውን አትልቀም። ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ መተው አለበት።
-
-
ኤርምያስ 49:9, 10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ
ጥቂት ቃርሚያ አያስቀሩም?
ሌቦች በሌሊት ቢመጡ፣
የሚዘርፉት የሚፈልጉትን ያህል ብቻ ነው።+
10 እኔ ግን ኤሳውን እርቃኑን አስቀረዋለሁ።
መደበቅ እንዳይችል
መሸሸጊያ ቦታዎቹን እገልጣለሁ።
-