የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 24
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

ዘዳግም የመጽሐፉ ይዘት

      • ጋብቻና ፍቺ (1-5)

      • ለሕይወት አክብሮት ማሳየት (6-9)

      • ለድሆች አሳቢነት ማሳየት (10-18)

      • የቃርሚያ ሕግ (19-22)

ዘዳግም 24:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ማቴ 5:31, 32፤ ማር 10:4, 11
  • +ሚል 2:16፤ ማቴ 1:19፤ 19:3-8

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    “ተከታዬ ሁን፣” ገጽ 104-105

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    12/2018፣ ገጽ 11

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    8/2016፣ ገጽ 10-11

    ኢየሱስ—መንገድ፣ ገጽ 222

    መጠበቂያ ግንብ፣

    9/1/2008፣ ገጽ 25

    8/15/1993፣ ገጽ 4-5

ዘዳግም 24:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 21:7

ዘዳግም 24:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 20:7፤ ምሳሌ 5:18፤ መክ 9:9

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    የስብሰባው አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች፣ 7/2021፣ ገጽ 7-8

ዘዳግም 24:6

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሰውየውን ሕይወት፤ የሰውየውን ነፍስ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:26, 27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ፣

    6/1/2014፣ ገጽ 7

    9/15/2004፣ ገጽ 26

ዘዳግም 24:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 37:28፤ 40:15
  • +ዘፀ 21:16
  • +ዘዳ 19:18, 19፤ 21:20, 21

ዘዳግም 24:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “የሥጋ ደዌ” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል ሰፊ ትርጉም ያለው ሲሆን የተለያዩ ተላላፊ የቆዳ በሽታዎችን ሊያመለክት ይችላል። ልብስንና ቤትን የሚበክሉ አንዳንድ በሽታዎችንም ሊጨምር ይችላል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 13:2, 15፤ ማር 1:44፤ ሉቃስ 17:14

ዘዳግም 24:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 12:10, 15

ዘዳግም 24:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:7, 8፤ ምሳሌ 3:27

ዘዳግም 24:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢዮብ 24:9, 10

ዘዳግም 24:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:26, 27

ዘዳግም 24:14

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “በደጆችህ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 25:39, 43፤ ምሳሌ 14:31

ዘዳግም 24:15

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ነፍሱ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:13፤ ኤር 22:13፤ ማቴ 20:8
  • +ምሳሌ 22:22, 23፤ ያዕ 5:4

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    1/2018፣ ገጽ 32

ዘዳግም 24:16

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ዜና 25:3, 4
  • +ሕዝ 18:20

ዘዳግም 24:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ወላጅ አልባ የሆነውን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 22:21, 22
  • +ዘፀ 22:26, 27

ማውጫዎች

  • የምርምር መርጃ

    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)፣

    2/2019፣ ገጽ 24-25

ዘዳግም 24:18

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:15

ዘዳግም 24:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 15:7, 10፤ ምሳሌ 11:24፤ 19:17፤ ሉቃስ 6:38፤ 2ቆሮ 9:6፤ 1ዮሐ 3:17
  • +ዘሌ 19:9፤ 23:22፤ ሩት 2:16፤ መዝ 41:1

ዘዳግም 24:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘሌ 19:10፤ ዘዳ 26:13

ተዛማጅ ሐሳብ

ዘዳ. 24:1ማቴ 5:31, 32፤ ማር 10:4, 11
ዘዳ. 24:1ሚል 2:16፤ ማቴ 1:19፤ 19:3-8
ዘዳ. 24:2ዘሌ 21:7
ዘዳ. 24:5ዘዳ 20:7፤ ምሳሌ 5:18፤ መክ 9:9
ዘዳ. 24:6ዘፀ 22:26, 27
ዘዳ. 24:7ዘፍ 37:28፤ 40:15
ዘዳ. 24:7ዘፀ 21:16
ዘዳ. 24:7ዘዳ 19:18, 19፤ 21:20, 21
ዘዳ. 24:8ዘሌ 13:2, 15፤ ማር 1:44፤ ሉቃስ 17:14
ዘዳ. 24:9ዘኁ 12:10, 15
ዘዳ. 24:10ዘዳ 15:7, 8፤ ምሳሌ 3:27
ዘዳ. 24:12ኢዮብ 24:9, 10
ዘዳ. 24:13ዘፀ 22:26, 27
ዘዳ. 24:14ዘሌ 25:39, 43፤ ምሳሌ 14:31
ዘዳ. 24:15ዘሌ 19:13፤ ኤር 22:13፤ ማቴ 20:8
ዘዳ. 24:15ምሳሌ 22:22, 23፤ ያዕ 5:4
ዘዳ. 24:162ዜና 25:3, 4
ዘዳ. 24:16ሕዝ 18:20
ዘዳ. 24:17ዘፀ 22:21, 22
ዘዳ. 24:17ዘፀ 22:26, 27
ዘዳ. 24:18ዘዳ 5:15
ዘዳ. 24:19ዘዳ 15:7, 10፤ ምሳሌ 11:24፤ 19:17፤ ሉቃስ 6:38፤ 2ቆሮ 9:6፤ 1ዮሐ 3:17
ዘዳ. 24:19ዘሌ 19:9፤ 23:22፤ ሩት 2:16፤ መዝ 41:1
ዘዳ. 24:20ዘሌ 19:10፤ ዘዳ 26:13
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ዘዳግም 24:1-22

ዘዳግም

24 “አንድ ሰው አንዲት ሴት ቢያገባ ሆኖም ነውር የሆነ ነገር አግኝቶባት ቅር ቢሰኝ የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት+ ከቤቱ ያሰናብታት።+ 2 እሷም ከእሱ ቤት ከወጣች በኋላ የሌላ ሰው ሚስት መሆን ትችላለች።+ 3 በኋላ ያገባትም ሰው ቢጠላትና የፍቺ የምሥክር ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ ቢያሰናብታት ወይም አግብቷት የነበረው ሁለተኛው ሰው ቢሞት 4 ከቤቱ አሰናብቷት የነበረው የመጀመሪያው ባለቤቷ ከረከሰች በኋላ እንደገና ሚስቱ አድርጎ እንዲወስዳት አይፈቀድለትም፤ ምክንያቱም ይህ በይሖዋ ፊት አስጸያፊ ነው። አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጣ።

5 “አንድ ሰው አዲስ ሙሽራ ከሆነ በሠራዊቱ ውስጥ ማገልገል የለበትም፤ ወይም ምንም ዓይነት ሌላ ሥራ ሊሰጠው አይገባም። ለአንድ ዓመት ያህል ከምንም ነገር ነፃ ሆኖ ይቆይ፤ በቤቱም ተቀምጦ ሚስቱን ያስደስታት።+

6 “ማንም ሰው ወፍጮን ወይም መጅን የብድር መያዣ አድርጎ መውሰድ የለበትም፤ ምክንያቱም የሰውየውን መተዳደሪያ* መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆንበታል።+

7 “አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ መካከል አንዱን አፍኖ በመውሰድ በደል ሲፈጽምበትና ሲሸጠው+ ቢገኝ አፍኖ የወሰደው ሰው ይገደል።+ ክፉ የሆነውን ከመካከልህ አስወግድ።+

8 “የሥጋ ደዌ* ቢከሰት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጧችሁን መመሪያዎች ሁሉ በጥንቃቄ ተከተሉ።+ እኔ የሰጠኋቸውንም ትእዛዝ በጥንቃቄ ፈጽሙ። 9 ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ መንገድ ላይ ሳላችሁ አምላካችሁ ይሖዋ በሚርያም ላይ ያደረገውን አስታውሱ።+

10 “ለባልንጀራህ ማንኛውንም ነገር ብታበድር+ መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ለመውሰድ ወደ ቤቱ አትግባ። 11 ውጭ ቆመህ ጠብቅ፤ ያበደርከውም ሰው መያዣ አድርጎ የሚሰጥህን ነገር ውጭ ድረስ ያምጣልህ። 12 ሰውየው ከተቸገረ መያዣ አድርጎ የሰጠህን ነገር አንተ ጋ አታሳድር።+ 13 ልክ ፀሐይ ስትጠልቅ መያዣውን ልትመልስለት ይገባል፤ እሱም ለብሶት ይተኛል፤+ ደግሞም ይባርክሃል፤ በአምላክህም በይሖዋ ፊት እንደ ጽድቅ ይቆጠርልሃል።

14 “ከወንድሞችህም ሆነ በምድርህ ይኸውም በከተሞችህ* ውስጥ ከሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች መካከል የተቸገረውንና ድሃ የሆነውን ቅጥር ሠራተኛ አታታል።+ 15 ደሞዙን በዕለቱ ስጠው፤+ ችግረኛ በመሆኑና ሕይወቱ* የተመካው በደሞዙ ላይ ስለሆነ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት ስጠው። አለዚያ በአንተ የተነሳ ወደ ይሖዋ ይጮኻል፤ አንተም በኃጢአት ትጠየቃለህ።+

16 “አባቶች ልጆቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም፤ ልጆችም አባቶቻቸው በሠሩት ነገር መገደል የለባቸውም።+ አንድ ሰው መገደል ያለበት በገዛ ኃጢአቱ ብቻ ነው።+

17 “የባዕድ አገሩን ሰው ወይም አባት የሌለውን* ልጅ ፍርድ አታዛባ፤+ የመበለቲቱን ልብስ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ።+ 18 አንተም በግብፅ ባሪያ እንደነበርክና አምላክህ ይሖዋ ከዚያ እንደተቤዠህ አስታውስ።+ እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው።

19 “በማሳህ ላይ ያለውን እህል በምታጭድበት ጊዜ በማሳው ላይ ነዶ ብትረሳ ያን ለመውሰድ አትመለስ። አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ እንዲባርክልህ+ ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ እንዲሆን እዚያው ተወው።+

20 “የወይራ ዛፍህን በምታራግፍበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ሙልጭ አድርገህ አታራግፈው። የቀረው ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ ይሁን።+

21 “ከወይን እርሻህ ላይ የወይን ፍሬህን በምትሰበስብበት ጊዜ ተመልሰህ ቃርሚያውን አትልቀም። ለባዕድ አገሩ ሰው፣ አባት ለሌለው ልጅና ለመበለቲቱ መተው አለበት። 22 አንተም በግብፅ ምድር ባሪያ እንደነበርክ አስታውስ። እኔም ይህን እንድታደርግ የማዝህ ለዚህ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ