መዝሙር 16:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 መቃብር* ውስጥ አትተወኝምና።*+ ታማኝ አገልጋይህ ጉድጓድ እንዲያይ* አትፈቅድም።+ መዝሙር 30:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ይሖዋ ሆይ፣ ከመቃብር* አውጥተኸኛል።*+ በሕይወት አቆይተኸኛል፤ ወደ ጉድጓድ* ከመውረድ አድነኸኛል።+ ኢሳይያስ 38:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 እነሆ፣ ሰላም ከማግኘት ይልቅ በጣም ተመርሬ ነበር፤አንተ ግን ለእኔ* ካለህ ፍቅር የተነሳ፣ከጥፋት ጉድጓድ ጠበቅከኝ።+ ኃጢአቴን ሁሉ ወደ ኋላህ ጣልክ።*+ የሐዋርያት ሥራ 2:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 አምላክ ክርስቶስን በመቃብር* እንደማይተወውና ሥጋውም እንደማይበሰብስ* አስቀድሞ ተረድቶ ስለ ትንሣኤው ተናገረ።+